የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/GP/104/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጣርማ በር መለያ ሰፌድ ሜዳ እና ለአደሽሁ ዳላ ሳምረ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ጄነሬተሮች ግዥ አስመልክቶ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም፡ –
Item No |
Description |
Qty |
1 |
Generator 200-249KW |
04 |
2 |
Generator 300-349kw |
02 |
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔሲፊኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት የመለዋወጫ ዋጋ ለይተው ለብቻ በዝርዝር ማቅረብ ይኖርባቸዋል ተለይቶ ያልቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሠፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራንሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይቻላል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሐምሌ 14/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሐምሌ 14/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info @dce-et.com
የድህረ ገጽ:-WWW.dce.et.com
ፖላቁ 3414 ፋክስ ቁ 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ