የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- DGE/EM/94/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለኢንሳ ዋና መ/ቤት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ዓይነት የswitch Box ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ ወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም:
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ ሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን ካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: እንዲሁም በቴክኒካል ሰነድ ማጠቃለያ ሠንጠረዥ ላይ ለሚወዳደሩበት ማቴሪያል የሚያቀርቡት ዕቃ ተመጣጣኝ ወይም (Equivalent) ከሆነ በግልፅ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል:: ናሙናን በተመለከተ ባቀረቡት ካታሎግ መሰረት እና በዋጋቸው የሚመረጡ ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው:: ሆኖም ከላይ መሟላት እንዳለበት ከተጠቀሱት ነጥቦች አንዱም ቢጐድል ተጫራቹ ቴክኒካል መስፈርቱን እንዳሟላ ተቆጥሮ ሠነዱ ተመላሽ ይደረግለታል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻየመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114403434/33
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72ፖላቁ 3414 ፋክስ ቁ 0114 4004/011442-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
WWW.dce-et.com/ E-mail:- info@dce-et.com