የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/86/2020 ይመለከታል
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለህጻናትና ወጣቶች ቲያትር ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል supply, install, commission, test telecom and data system ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለሚሳተፉባቸው እቃዎች ‹‹Manufacturer authorization letter” እና የታደሰ 3rd party product quality certificate” ለሁሉም ለሚሳተፍበት እቃዎች ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት::
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ አይነት ዋጋ ብቻ ነው:: በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት የምህንድስና ዕቃዎች ግዥ ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታው ለተዘረዘሩት ዕቃዎች ብዛት (Quantity) በሙሉ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 23/2012 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሰኔ 23/2012 ከቀኑ 8፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖረሳ ግቢ
ድህረ ገጽ:- WWW.dce.gov.et.com / www.dce.et.com ኢሜል :- INFO@dce-et.com