የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሚሰራቸው ለአድሽሁ ደላ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እና ለጨልጨል ግድብ አገልግሎት የሚውሉ Hand Held Communication Radio (VHF) with Accessories ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- DCE/EM/36/2020

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሚሰራቸው ለአድሽሁ ደላ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት እና ለጨልጨል ግድብ አገልግሎት የሚውሉ Hand Held Communication Radio (VHF) with Accessories ግዥ አስመልክቶ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

1. ተጫራቾች በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት   ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ ታክስ ክሊራንስ  ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ተጫራቾች ከኢትዮጵያ ፊደራላዊ ሪፖብሊክ ኮሚኒኬሽን ባለሥልጣን የሬድዮ መገናኛ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለበት፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔሲፊኬሽን መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥ የስራ ሂደት ቲም ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡

6. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃዎች ከታሎግ የሶስተኛ ወገን ማረጋገጫ፣ የጥራት ማረጋገጫ (Quality Certificate) እና በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ላይ ለይቶ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መጋቢት 16/2012 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸል፡፡

8.   ጨረታው መጋቢት 16/2012 ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጥዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

9. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

                 አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ

                     የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34

                     ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72

                     E-mail አድራሻ፡- info @dce-et.com

                     የድህረ ገፅ አድራሻ፡፡-WWW.dce.et.com

                     ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46

                     ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ