የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የመለዋወጫ ዕቃዎች የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር
ንብ/005/2012
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ በሚገኘው የመለዋወጫ ግ/ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ መለዋወጫ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፤ በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::
- LOT 1- የማሽነሪ መለዋወጫ .
- LOT 2- የከባድ ተሽከርካሪ መለዋወጫ
- LOT 3- የቀላል ተሽከርካሪ መለዋወጫ
- LOT 4- ጎማና ባትሪ
- LOT 5- መፍቻዎችና ቱልስ
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን መለዋወጫዎች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ጧት ከ3፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከ8፡00 እስከ 10፡00 ቃሊቲ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ መለዋወጫ ዕቃ ግ/ቤት በአካል በመሄድ መመልከት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለአንድ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አቅርቦትና ግዥ የሥራ ሂደት ቢሮ መግዛት ይቻላል::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 25,000/ሃያ አምስት ሺህ/ ሰባንክ የተረጋገጠ ቼክ ( ሲፒኦ) በድርጅታችን ትክክለኛ ስም “መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በሚል አስርተው ሲፒኦ’ውን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ የጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤
- ጨረታው ግንቦት 11,2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል:: ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ግንቦት 11/2012 ዓ.ም. ከጠዋቱ – 4፡00 ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያሸነፉበትን ክፍያ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተጨምሮበት ለድርጅቱ ፋይናንስ ቡድን ገቢ በማድረግ በጨረታ ያሸነፉበትን መለዋወጫዎች ማንሳት ይኖርባቸዋል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጨማሪ ማብራሪያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ስልክ ቁጥር
011-4-42-22-60/ 011-4-42-22-70
► 011-4-42-22-71/ 011-4-42-22-72