የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/BM/119/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ለድሬዳዋ አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ዓይት የ “Light Protection System as per attached specification “ ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ በተጫራቾች መመሪያ ተራ ቁጥር 7.3 እና 7.4 በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ ሥራ ሂደት ኬዝ ቲም ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ኦርጅናል ወይም የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት ኮፒ ካታሎግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ወይም በጨረታ መክፈቻ ቀን በካታሎጉ ላይ የሚወዳደሩበትን ዕቃ ለይቶ በማመልከት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- እንዲሁም በቴክኒካል ሰነድ ማጠቃለያ ሰንጠረዥ ላይ ለሚወዳደሩበት ማቴሪያል የሚያቀርቡት ዕቃ ተመጣጣኝ ወይም (Equivalent) ከሆነ በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል።
- ናሙናን በተመለከተ ባቀረቡት ካታሎግ መሠረት እና በዋጋቸው የሚመረጡ ተጫራቾች ናሙናን እንዲያቀርቡ ሲጠየቁ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ሆኖም ከላይ መሟላት እንዳለበት ከተጠቀሱት ነጥቦች አንዱም ቢጎድል ተጫራቹ ቴክኒካል መስፈርቱን እንዳላሟላ ተቆጥሮ ሰነዱ ተመላሽ ይደረግለታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተጠቀሰው ብዛት (Quantity) መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ነሐሴ 12 ቀን 2012 ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ