የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/HIV/88/2020
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ለአምቦ ወሊሶ የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት ግንባታ የማማከር አገልግሎት የሚውል ‹‹Consultancy Service for general STD and HIV/AIDS Aleviation measures” ግዥ ለመፈጸም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
ስለሆነም፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፣ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ እና በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችላቸው ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡት ገንዘብ መጠን ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) መሆን አለበት::
- አንድ ተጫራች መወዳደር የሚችለው በአንድ አይነት ዋጋ ብቻ ነው:: በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መስሪያ ቤት ምህንድስና ዕቃዎች ግዥ ኬዝ ቲም ሲሮ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ሰኔ 18/2010 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሰኔ 18/2012 ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል::
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡– የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34/33 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ. 0114-40-04-71/0114-42-07-46
ወሱ ሰፈር ያቀድሞው ኖሬሳ ግቢ
ድህረ ገፅ፡– WWW.dce.gov.et.com ኢሜል፡– INFO@dce-et.com