House and Building Foreclosure / House and Building Sale

የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ 

የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ትዕግስት ከሳ እና ስፍ/ባለዕዳ አቶ ሙሉጌታ በየነ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ ቤት በመ/ቁጥር/130804፤32030 በ09/02/2010 እና በ04/05/2010 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 13 አያት ግራውንድ በሚባል ሪል እስቴት ውስጥ የተሰራ እና ቁጥሩ 26-10 የሆነ መኖሪያ ቤት የካቁ AA000051305603 የተመዘገበ ካርታ ያለው የቦታው ስፋት 400 ካሜ የቤቱ ስፋት 242.50 ካሜ የሆነው ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 970,000.00 (ዘጠኝ መቶ ሰባ ሺ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ለጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል። የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፈዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት ሰሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት ሰፈፍ ሴቶች ፍርድ እፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁጉድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬከቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።

የፈራል ፍርድ ቤቶች

የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት