ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በከሣሽ የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም መሃልሜዳ ቅርንጫፍ እና በተከሣሽ ወ/ሮ ታደለች ቸርነት መካከል ስላለው የገንዘብ ክስ ክርክር ጉዳይ ለፍርድ ማስፈፀሚያ ይሆን ዘንድ በተከሣሽ ስም ተመዝግቦ የሚገኘውን በመሃል ሜዳ ከተማ ቀበሌ 03 ክልል ውስጥ በካርታ ቁጥር 34/መ/ሜ/ቴ/01/86 የሆነውን መኖሪያ ቤት በግምት መነሻ ዋጋ ብር 336,223.20 /ሶስት መቶ ሠላሣ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ሃያ ሶስት ብር ከሃያ ሣንቲም/ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በጨረታ እንዲሸጥ ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜው ውስጥ ይሆናል ፡፡
- ንብረቱን ለመሸጥ ምክንያት የሆነው እዳ ለማስከፈል ነው::
- በሐራጅ የተሸጠው ንብረት ዋጋው በሙሉ የሚከፈለው ገዥው ንብረቱን መግዛቱ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ይሆናል ::
- ገዥው በጨረታ ለገዛው ንብረት ዋጋውን ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ወይም በህግ በተወሰነው በዚሁ የሽያጭ ማስታወቂያ ላይ በተገለፀው መሠረት ዋጋውን ያላስቀመጠ እንደሆነ ሽያጩ ይሠረዛል በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ/429/2/ መሠረት ለሃራጅ ማስታወቂያው የተደረገውን ወጪ እንዲከፍል ይገደዳል፡፡
- የሐራጅ ማስታወቂያውን ለማቋረጥ የሚቻልበት የተሻለ መንገድ ካለ የጨረታ ማስታወቂያው በማንኛውም ጊዜ ሊቋረጥ ይችላል፡፡
የሰ/ሸዋ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት
ደ/ብርሃን