በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2013 በጀት ኣመት
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችን፣
- የጽዳት እቃዎችን እና
- የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቶች:-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተእታ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማስረጃ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 5000/አምስት ሺህ ብር/ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በጽ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ተጫራቶች በጨረታው ያሸነፉበትን እቃ ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- አድራሻ፡-ጅማ ከተማ
- ቦታው፡- ጅማ ሙዚየም አጠገብ ስልክ ቁጥር፡- 047-111-05-21/047-111-12-58/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፣
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ
ዋስትና ኤጀንሲ ደቡብ ምዕራብ
ሪጅን ጽ/ቤት