Aluminium Products / Disposal Sale / Other Metals / Other Sales / Spare Parts and Car Decoration Materials / Steel Raw Materials and Products / Tyres & Battery

የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የተለያዩ እቃዎችን መሸጥ ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

 • የተለያዩ የቁርጥራጭ ብረታ ብረት ዓይነቶች ማለትም ቁርጥራጭአልሙኒየም፣ ስቲል፣ አዳዲስ እና ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችበግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር PPPDS/NVP4FB/03/01/2013
 • የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ንብረትነታቸው በአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሆኑ የተለያዩ ቁርጥራጭ(ዲዛ) (አልሙኒየም) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 6000 ኪሎ ግራም፣ቁርጥራጭ ብረቶችና ያገለገለ ቆርቆሮዎች ጠቅላላ ክብደቱ በግምት10,000 ኪሎ ግራም፣ አዲስ አበባ ዪኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ ካስት አይረንጠቅላላ ከብደቱ በግምት 2000 ኪሎ ግራም፣ ስቲል ጠቅላላ ክብደቱበግምት 45,000 ኪሎ ግራም፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆኗል ግቢ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩአሮጌ ብረታ ብረቶች (stecl) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 100,000 ኪሎግራም፣ የሊፍት ብረት (steel) ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 50,000 ኪሎግራም፣ አልሙኒየም ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 40,000 ኪሎ ግራም፣የትራንስፖርት ባለስልጣን የሆኑ የተለያዩ ቁርጥራጭ አልሙኒያም ጠቅላላከብደቱ በግምት 3000 ኪሎ ግራም፣ የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ በግምት 1500ኪሎ ግራም ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና የኢፌዲሪ ፖለስ ኮሚሽን ጤናአገልግሎት ም/ዘርፍ ስቲል አይረን ጠቅላላ ክብደቱ በግምት 6,000 ኪሎግራም ባሉበት ሁኔታና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላትቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
 1. በጨረታው የሚወዳደሩት ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸውሆኖ ሠነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይምመታውቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡
 2. . በገንዘብ ሚኒስቴር ቁጥር 2 ግቢ ውስጥ በሚገኘው የመንግሥትግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ህንፃ ቁጥር 5 ቢሮ ቁጥር001 በመምጣት የቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ዝርዝር መረጃ፣የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድየማይመለስ ብር 30.00 /ሰላሳ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፣
 3.  ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓትባለው ጊዜ ውስጥ ለሽያጭ የቀረቡ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን እናጎማዎችን ከላይ በተጠቀሰው መ/ቤት በመሄድ መመልከት ይችላሉ፣
 4. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ መ/ቤት የቁርጥራጭብረታ ብረት ዓይነት ማለትም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስናኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ቁርጥራጭ ብረቶችና ያገለገሉ ቆርቆሮዎችብር 20,000.00፣ዲዛ (አልሙኒየም) ብር 24,000.00፣ በአዲስአበባ ዪኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድሆ/ል ጊቢ ውስጥ አሮጌ ብረታ ብረት (steel) ብር 200,000.00፣ሊፍት ብረት(steel) ብር 250,000.00፣አልሙኒየም ብር240,000.00፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ ካስት አይረንብር 5,000.00፣ስቲል ብር 90,000.00 ለትራንስፖርት ባለስልጣንቁርጥራጭ አልሙኒየም ብር 18,600.00፣ ለሐዋሳ ዩነቨርሲቲቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ብር 2,250.00፣ የኢፌዴሪ ፖሊስኮሚሽን ጤና አገልግሎት ም/ዘርፍ ብር 12,000.00 የጨረታማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝናበታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድአገልግሎት ቢሮ ቁጥር 001 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
 5. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርቱ ዋጋና የተሟላ የጨረታማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትንአሟልቶ መገኘት ነው፡፡
 6. ከላይ በተራ ቁጥር 4 የተገለፀውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡ ሌሎች ነጥቦችን ያላሟላ ተጫራችከጨረታው ውድቅ ይደረጋል።
 7. የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፣
 8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓትተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በመንግሥትግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽይከፈታል፡፡ ሆኖም የመከፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላትቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹበራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀርየጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
 9. አሸናፊ ተጫራቾች የአሸናፊዎች ዝርዝር ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር ከ7 /ሰባት/ ተከታታይ የሥራቀናት በኋላ ባሉት 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥየውል ማስከበሪያ የውል ዋጋውን 10 በመቶ በማቅረብ ከአገልግሎቱጋር ውል መፈራረምና፤ በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠው የእያንዳንዱየቁርጥራጭ ብረታብረት ዓይነት ግምታዊ ጠቅላላ መጠን ተወስዶባሸነፉበት የ ኪሎ ግራም ዋጋ መሰረት ተሰልቶ የቁርጥራጭ ብረታብረቱን ጠቅላላ ዋጋ በመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎትስም CPO አዘጋጅተው መክፈል አለባቸው:: በተጨማሪምየቁርጥራጭ ብረታ ብረቶቹ ግምታዊ መጠን በርክክብ ወቅት ስሚዛንፕሪንት አውቱ ንባብ ከሚገኘው ትክክለኛ የቁርጥራጭ ብረታ ብረትመጠን ጋር የሚኖረው ልዩነት ታስቦ አሸናፊው ተጫራች ተጨማሪክፍያ የሚኖርበት ከሆነ የውሉ ጊዜ ከመጠናቀቁ በፊት በልዩነትየሚኖረውን ሂሳብ መክፈል ያለበት ሲሆን ከአገልግሎቱ ተመላሽሊደረግለት የሚገባ ገንዘብ ካለም በትክክለኛው የገንዘብ መጠን ልክሲፒኦ አሰርቶ በመምጣትና በመክፈል ቀደም ሲል ግምታዊ መጠኑተሰልቶ ያስያዘው የክፍያ ሲፒኦ በአገልግሎቱ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
 10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ቁርጥራጭ ብረታ ብረት በራሳቸው ወጪበማጓጓዝ፣ የሚዛንና ሌሎች ወጪዎች በመሸፈን ቁርጥራጭብረታብረቱ ከሚገኝበት ሥፍራ ቅርብ በሆነ ፕሪንት አውት ማውጣትበሚችል የመንግስት የምድር ሚዛን በማስመዘን ውል በፈረሙ በ20የሥራ ቀናት ውስጥ ቁርጥራጭ ብረታብረቱን በማንሳት ማጠናቀቅአለባቸው፡፡
 11. አገልግሎቱ ባወጣው ጨረታ ሰነድ በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
 12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-154-04-25 ወይም011-122-37-08/36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
 13. አገልግሎቱ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆንበማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

የመንግሥት ግዥና ንብረት

ማስወድ አገልግሎትአዲስ አበባ