የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በሽያጭ
ወደ ግል ይዞታ ለማዛወር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር – 001/2019-2020
- የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ቀጥሎ የተመለከተው እርሻ ሙሉ በሙሉ ባለቤት ነው፡፡
- የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በመቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 445/2011 በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረትከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰውን ድርጅት ለመምራትና ለማስፋፋት ፈቃደኛ ለሆኑና አቅም ላላቸው ባለሃብቶች በሽያጭ የጨረታ 001/2019-2020 ለማስተላለፍ ይፈልጋል
- ለሽያጭ የቀረበ ድርጅት፡
- አባያ እርሻ ……………አባያ/ወላይታ ሶዶ
4. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ አፈጻጸም የተዘጋጁትን የጨረታ ሠነዶች ገርጂ በሚገኘው ውሃ ሥራ ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ህንጻ የመንግሥት የልማትድርጅቶች ይዞታናአስተዳደር ኤጀንሲ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ተመላሽ የማይደረግ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ወይም የዚህን ተመጣጣኝ የሆነ በአሜሪካን ዶላር በመክፈል ከሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሠዓት መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ፕሮፖዛላቸውን ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ፣ የተጫረቱበትን ድርጅት ስምና የጨረታ ቁጥሩን በመጥቀስ በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፕ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው፡፡
7. ጨረታው ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀኑ በ9፡15 ሰዓት በ2ኛ ፎቅ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
8. ተጫራቾች ፕሮፖዛል የሚያቀርቡበት ቀን እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓም ከቀኑ በ9፡00 ሲሆን ከዚህ ዘግይቶ የመጣ ፕሮፖዛል ተቀባይነት የለውም፡፡
9. ኤጀንሲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
10.ተጫራቾች የጨረታ ፕሮፖዛላቸውን የሚያቀርቡት በሚከተለው አድራሻ ይሆናል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ
ስልክ፡– 011 8 69 37 29/0118693781 ፖሣቁ ከ11835
ገርጂ በቀድሞው ኢምፔሪያል ሆቴል ፊት ለፊት ባለው ወሃ ሥራዎች
ዲዛይንና ቁጥጥር ድርጅት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 204 አዲስ አበባ፣ ኢ ትዮጵያ
በጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019-2020 መሠረት
ለአባያ እርሻ ቀረበ የጨረታ ፕሮፖዛል በማለት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ