ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግዥና/ንብ/አስ/ቡ/ጨ/ቁ /02/13
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ት/ብ/ፅ/ቤት በግዥና ንብረት አስ/ቡድን በ2013 በጀት አመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ፡
- ሎት1፡– የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት2፡– ኤሌክትሮኒክስ ፣
- ሎት3፡– የኤሌክትሪክ እቃዎች
- ሎት4፡– የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት 5፡–የተሽከርካሪ ጎማና ከመነዳሪ፣
- ሎት6፡– ፈርኒቸር
- ሎት7፡– የስፖርት ማቴሪያል
- ሎት8፡– ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት
- ሎት9፡– ቆዳ እና ቆዳ ውጤቶች
- ሎት10፡– የተለያዩ ሞዴል ላላቸው የመኪና መለዋወጫ ስፔር ፓርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡
- በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር/ ያላቸው
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከሚያስገቡት የመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው፡፡ ጨረታ ማስከበሪያው የሚሰላው በአርቴሜቲክ ቼክ ስሌት በሚገኘው ጠቅላላ ዋጋ ሲሆን ከላይ ከተገለፀው ከ1% በታች መሆን የለበትም፡፡
- ተጫራቾች በአንድ ሎት ውስጥ ከተዘረዘሩት የእቃ ዓይነቶች መካከል ከፋፍለው መጫረት አይቻልም፡፡
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ የራሳቸውን ስምና ፊርማ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዳቸው ላይ በአንድ ኦርጅናል ፖስታ ብቻ በማድረግ፣ በመሙላት እና በመፈረም በሚያስገቡት ፖስታ ላይ የራሳቸውን ስም፣ ፊርማ ፣ ቀን፣ ስልክ ቁጥር ፣አድራሻ ተፅፎበት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50.00 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል ከመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብብር ጽ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
- መስሪያ ቤቱ ከሚገዛቸው እቃዎች ላይ 20 በመቶ የመጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ/ያልተካተቱ ጉዳዮች ካሉ በግዥ መመሪያው እና አዋጁ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጭ ወረዳው ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 672 93 11 ደውለው ይጠይቁ
የመንዝ ላሎ ምድር ወረዳ ገ/ኢ/ል/ትብ/ፅ/ቤት/
ወገሬ