ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንገስታዊ የሆነው የልማት ድርጅት ሲሆን ከ2ዐ1ዐ-2012 ዓ/ም ድረስ ያሉ የሂሳብ ሰነዶች በውጭ ኦዲተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት
- ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በመሙላት በስም በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ቢቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ::
- ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል:: ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመከፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን ከመከፈት አያስቀረውም::
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበ ንግድ ፈቃድ የነጋዴነት መለያ ቁጥር የዘመኑኑ ግብር የገበሩና የቫት ተመዝግቢ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በመቅረብ በነፃ መውሰድ ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 1ዐ በመቶ በሁኔታ ላይ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበት ዋጋ ከ200 ሽህ በላይ ከሆነ የቫት ሰርተፊኬት ማያያዝ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉ 7 የስራ ቀናት ውስጥ ውል በመያዝ ስራውን መስራት ይጠበቅባቸዋል::
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት የመንግስት የልማት ድርጅቶችን ሂሳብ መርምረው በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0930958351 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
- ኢንተርኘራይዙ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጫራታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ