የጨረታ ማስታወቂያ
የመቱ ካርል ሪፈራል ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን የምግብ አቅርቦት አገልግሎት መስጠት የሚችሉትን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በስራ ዘርፍ የስራ ፍቃዱ ያለው::
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአሸነፈበትን የምግብ አቅርቦት ከቦታው ደርሶ ምግብ ማቅረብ የሚችል፡፡
- በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 50.00 (ሃምሳ ብር ) በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን የጨረታውን ሰነድ መቱ ካርል ሆስፒታል አስተዳደር ቁጥር 11 በመምጣት መውሰድ ይቻላል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀን የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ ጨረታው ሰነድ ገብቶ በ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ጨረታ ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡– 0471410744
የመቱ ካርል ሪፈራል ሆስፒታል