ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመቄት ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ለመቄት ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች በመደበኛ ፣ በመደበኛ ካፒታል በጀት እና መደበኛ ባልሆኑ
- ሎት 1 የህንፃ መሣሪያ
- ሎት 2 አፍሪዲ ፓምፕ
- ሎት 3 ብሎኬት ጥቅል ድምር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች
ማለትም፡-
- ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ጨረታው ከ200 ሺህ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመሂ 1 ማስያዝ የሚችል፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም ዓይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው፣
- የጨረታ ሰነዱ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በሰም በታሸገ ፖስታ ማስገባት የሚችሉ፡፡ በሰም የታሸገ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ባለመታሸጉ ጨረታውን ውድቅ አያደርገውም፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ጨረታ በድህረ ገጽ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን ሁልጊዜ በስራ ቀናት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነዱ ይሸጣል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ቀን 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለዚህ መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መ/ወ/ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በመቅረብ የማይመለስ ብር 20 በመክፈል መግዛት የምትችሉ ሲሆን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሣሰቢያ፡- የጨረታ ሰነዱ የሚገባው ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 13 በሚገኘው ሣጥን ውስጥ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0332110091/90 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የመቄት ወረዳ ገ/ኢ/ትብብር ጽ/ቤት