የጨረታ ማስታወቂያ
የመስከረም አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ/ደ/ት/ ቤት የተለያዩ እቃዎች ቴሌቭዥን ፍላት ስክሪን 54 ኢንች ፣ ላፕቶፕ፣ የፕላስቲክ የመሬት ምንጣፍ፣ የዲሽ ዲኮደር HD፣ ኤክስተርናል ሀርድ ዲስከ 500 GB አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል ፡፡
ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለመወዳደር ይችላሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት (CPO) 5000 ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎች እስከ ት/ቤቱ ማድረስ አለበት፡፡
- ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ፡ በ4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቶች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም::
- አሸናፊ ተጫራቾች 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ት/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ በፖስታ ታሽጎ ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ድርጅቱ፡ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0118-12-40-06 እና 0118-59-14-75 በመደወል እንዲሁም በአካል ጊቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ጀርባ በአታ ጤና ጣቢያ አጠገብ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ፡፡
አድራሻ
- በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም አጸደ ህጻናትና የመጀ/ደ/ት/ ቤት
- ጊቢ ገብርኤል ጀርባ በአታ ጤና ጣቢያ አጠገብ
- ስልክ ቁጥር 011-5591-475 እና 011-124-006
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር
በአራዳ ክ/ከተማ ትምህርት መምሪያ
መስከረም አጸደ ህጻናትና