ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2013 በጀት ዓመት ለወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች መንገድ ስራ የሚሆን ሬድ አሽ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የዕቃው አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር የያዘውን ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የዕቃውን እስፔስፊኬሽን በተገለፀው መሰረት ተሞልቶ እንዲገለጽና የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የመ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 10000/አስር ሺህ ብር ብቻ/በባንክ በተመሰከረለት/CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በተዘጋጁት ዝርዝር እስፔስፊኬሽን ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል።
- የተጫራቾች አለመኖር ፖስታው ተሟልቶ እስከተገኘ ድረስ ጨረታውን አያስተጓጉልም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0461151102 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደቡብ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት በጉራጌ ዞን የመስቃን ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት