ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመርዓዊ ከተማ ውሃ እና ፍሣሽ አገልግሎት ጽ/ቤት የውሃና የጽዳት ዕቃዎችን
- ሎት 1 የውሃ መያዣ ጀሪካ/tanker/
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች ለ2013 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ስለዚህ በጨረታ መወዳደሪያ የምትፈልጉ፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችል፣
- የግዥ መጠኑ ከ50 ሺህ ብር በላይ ከሆነ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ (በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16 ተከታታይ ቀን ድረስ ማለትም እስከ 4፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ በ4፡ 30 ይከፈታል፡፡
- የሚገዙ ማቴሪያሎች አይነት እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላይ ይከፈታል ነገር ግን ተጫራቾች በጨረታ መክፈቻ ቀን ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ማቴሪያሎች በራሱ ወጭ ሸፍኖ ዕቃው በተጠየቀው መሰረት በባለሙያ እየተረጋገጠ ንብረት ክፍል ድረስ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራጭ የጨረታ ሠነዱን ኦርጅናል ኮፒ እንዲሁም ሲፒኦ ብሎ በመለየት እና በአንድ ፖስታ በማሸግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ቦታ ላይ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 30 በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
- የጨረታ መክፈቻ የመጨረሻ ቀን በካላንደር ዝግ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ቀን ይሸጋገራል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መወዳደርና ባላቸው ንግድ ፍቃድና ቲን በሙያው ብቻ ነው፡፡
- አሸናፊው ማሸነፉ ከተረጋገጠበት የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- ከጨረታው ሰነድ ላይ ያልተገለፀ ሂደት ካለ በግዥ መመሪያ መሠረት የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- የመርዓዊ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ከሚገዛቸው ማቴሪያሎች ላይ 20 በመቶ የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ባለው የስራ ፈቃድ መሰረት በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሞላት አለበት፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ መረጃ ከፈለጉ መርዓዊ ከተማ ውሃ አገልግሎት የገ/ግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ወይም በስልክ ቁጥር 0583300146/0583300082 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የመርዓዊ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት