Land Lease & Real Estate

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

የመሬት ሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በምስ/ጎ/ዞን በደ/ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 1 እንዲሁም በክልሉ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመፍቀድ የወጣ የአፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 1/2005 ክፍል4 መሰረት 1ኛ ዙር ለመኖሪያ አገልግሎት የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል:: በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ሁሉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይየስራ ቀናት በመምጣት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ 200 ብር በመክፈል በደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በመቅረብ መግዛት የሚቻል መሆኑንእየገለጽን::

 1.  ቦታውን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል::
 2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ የተጫረቱበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘው ውጤት 5 በመቶ እና ከዚያ በላይ በዝግ አካውንት ቁጥር በማስገባት በባንክ የተመሰከረለት ሰነድከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 3. ተጫራቾች በሚዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ሞልተው ጨረታው በወጣ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ እስከ ቀኑ 11፡00 ማስገባት ይጠበቅባቸዋል::
 4. በመጀመሪያ ዙር ለአንድ ቦታ ከሶስት ተጫራች በታች ከቀረበ በጨረታው የቦታውን አሸናፊ መለየት አይቻልም::
 5. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸው ፊርማቸውን የስልክ ቁጥራቸውን እና አድራሻቸውን በሁሉም ገጽ ላይ ማኖር ይጠበቅባቸዋል::
 6. . አሸናፊ ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በአካል ቀርቦ በ10 ቀን ውስጥ ውል መዋዋል አለበት::
 7. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረትበትን የቦታ ዋጋ በፊደል እና በአሃዝ መሙላት ይኖርበታል:: በፊደል እና በአሃዝ በተፃፈው መካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተፃፈው ተቀባይነት ይኖረዋል::
 8. በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በግልጽ እና ሊታይ በሚችል ጽሁፍ መሞላት ያለበት ሲሆን ስርዝ ድልዝ እና ሊለይ የማይችል የዋጋ መሙያ ከተገኘ ከጨረታ ውጭ የሚደረግ ይሆናል::
 9. በጨረታው የውጭ አገር ዜጎች መሳተፍ አይችሉም::
 10. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾት ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም እራሳቸውን ከጨረታው ማግለል አይችሉም::
 11. ተጫራቾች ሰነዳቸውን በጨረታ ሳጥን ካስገቡ በኋላ በመሰረዝ በምትኩ ሌላ ሰነድ ማስገባት አይችሉም::
 12. ለአንድ ቦታ አንድ ተጫራች ከአንድ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም::
 13. ለጨረታ በቀረቡ ቦታዎች ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ እና ሌሎች የሚገቧቸውን ግዴታዎች ሞልተው የሚቀርቡበት ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ቅጽ አማካኝነት ብቻ ነው::
 14. . ከላይ የተገለፀው እንደተጠበቀ ሆኖ የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ በጽ/ቤቱ በኩል ካጋጠመ እና ለመደበኛ ጨረታ የቀረበው ቦታ በ3 ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት የተሸጠው ሰነድሲነፃፀር ከ50 በመቶ በታች ሆኖ ሲገኝ ወይም በቀረበው ቦታ በቂ ተጫራቾች ያልተሳተፉ መሆኑን ሲታመንበት ለተጨማሪ 7 የስራ ቀናት የሚቆይ ሰነድ ሽያጭ ማቅረቢያ ጊዜ እና ጨረታው የሚከፈትበትንተለዋጭ የስራ ቀን እና ሰዓት በልዩ ልዩ መንገድ የሚያሳውቅ ይሆናል::
 15. ተጫራቾች ሰነድ በሚገዙበት ጊዜ ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
 16. የጨረታ ሳጥኑ የሚታሸገው ጨረታው በወጣ በ10ኛው ተከታታይ የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 በጨረታ አስፈፃሚ ቡድን እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይሆናል::
 17. ጨረታው የሚከፈተው ሳጥኑ በታሸገ በቀጣዩ ቀን ወይም በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ደ/ኤልያስ ብልጽግና ጽ/ቤት አዳራሽ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ይሁን እንጅተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም እንኳ ጨረታው በዕለቱ የሚከፈት ይሆናል::
 18. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
 19. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 250 02 30 መጠየቅ ይቻላል::

የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት