በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቅጽ
የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2013 ዓ/ም
በአዲስ አበባ ከተማ የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር /ጤ/ጽ/ቤት ወረዳ 10 የመሪ ጤና ጣቢያ የ2013 ዓ/ም የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት በግልፅ ጨረታ ግዥ ለመፈፀም ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት እቃዎች
- ሎት 1- የደንብ ልብስ፣
- ሎት-2 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት -3 የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት-4 የህትመት ስራዎች ፣
- ሎት – 5 አላቂ የህክምና ዕቃዎች ፣
- ሎት – 6 ልዩ ልዩ ዕቃዎች ፣
- ሎት -7 የጥገና እቃዎች ፣
- ሎት– 8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች ጀኔሬተር እና የሳር ማጨጃ ማሽን ጨምሮ መ/ቤቱ ባወጣው እስፔስፍኬሽን መሰረት ፣
- ሎት 9 ቋሚ የህክምና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች
1.ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3 የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
4 የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. በማንኛውም ግልፅ ጨረታ ላይ ያልታገዱ መሆን አለበት ።
6. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማቅረብ አለባቸው።
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር
|
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ |
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
ብር 3000.00 |
ሎት 2 |
አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች |
ብር 2,000.00 |
ሎት 3 |
የጽዳት ዕቃዎች |
ብር 2,000.00 |
ሎት 4 |
የህትመት ስራዎች |
ብር 3,500.00 |
ሎት 5 |
አላቂ የህክምና ዕቃዎች |
ብር 4000.00 |
ሎት 6 |
ልዩ ልዩ ዕቃዎች |
ብር 1,000.00 |
ሎት 7 |
የጥገና ዕቃዎች እና የጥገና ስራዎች ጭምር |
ብር 3000.00 |
ሎት 8 |
በቋሚ የቢሮ እቃዎች |
ብር 9000.00 |
ሎት 9 |
ቋሚ የህክምና እቃዎች |
ብር 9000.00 |
7. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100.00/ አንድ መቶ ብር / በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ ።
8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10/አስር /ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በመሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 52 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ።
9. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጥዋቱ 2፡30 እስከ 7፡50 ድረስ ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን ከሰአት በኋላ 8፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እና በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው ።
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ ዕቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው በተጨማሪም በፎቶ /በማንዋል/ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ።
12. በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት