የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት ከዚህ በታች ለተጠቀሱት ዕቃዎች የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች የሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት1፦ የጽዳት አላቂ ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 2፡– የጽህፈት መሣሪያና ተያያዥ ዕቃዎች
- ሎት 3: የመኪና ጎማ ግዥ (ለ2ኛ ጊዜ የወጣ)
- ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘመኑ ግብር የተከፈለበት እና የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነዱን ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 50.00/ሃምሳ ብር/ በመክፈል በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናቶች ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 1 በመቅረብ ለሚፈልጉት የሰነድ ዓይነት ክፍያ ፈጽመው ሰነዱን ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 46 ከግዥ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሱት፡– ለሎት1 የጽዳት አላቂ ዕቃዎች ግዥ ብር 3,000.00 (ሶስት ሺ ብር ብቻ)፡ ለሎት 2 የጽህፈት መሣሪያና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ ብር 3,000.00 (ሶስት ሺ ብር ብቻ፡ እና ለሎት 3 የመኪና ጎማ ግዥ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ CPO፡ ቢድ ቦንድ እና በጥሬ ገንዘብ ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እንደታወቀ ውል ለመዋዋል የሚያስችል ለአሸነፈው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው የመጫረቻ ሰነዶች ፋይናንሻል፡ ቴክኒካል፡ ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀናት ጠዋት ከ4፡00 ሰዓት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 46 ከግዥ ክፍል አካባቢ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ የመጫረቻ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለሁሉም ሎቶች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለዚሁ በተዘጋጀው አዳራሽ በግልጽ ይከፈታል፣
- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እንገልፃለን።
- ሲፒኦ ወይም ቢድቦንድ ሲዘጋጅ፡– በአማርኛ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት በእንግሊዝኛ Secretariat of The House of peoples Representative በሚል መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111-24-1037 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፣
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽ/ቤት