የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐይቅ ከተማ አስተዳደር ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2013 በጀት ዓመት ለሐይቅ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች ሥራ አገልግሎት የሚውሉ፤
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
- የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎችና መሣሪያዎች
- የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች
- የደንብ ልብስ ( ጫማ፤ የተዘጋጁ ልብሶችና ቴትረን 6000)
- የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ፤
- የህንፃ መሣሪያ ዕቃዎች
- የጽህፈት መሣሪያዎች
- የተለያዩ ህትመቶች
- የእንስሳት መድሃኒቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት:
- በዘመኑ የታደሠ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ( TIN ) ያላቸው ::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ/ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 80.00 ( ሰማንያ ብር ) በመክፈል ሐይቅ ከተማ አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል ::
- የጨረታ ሰነዱን ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሐይቅ ከተማ አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር/ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይ/ንብ/አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል የማይችል ሲሆን፤ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጐ ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ( ባይገኙም ይከፈታል) የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይፈፀማል::
- አሽናፊው የሚለየው በሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው::
- ጽ/ቤቱ እንደ በጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት የሚቀርቡትን ዕቃዎችን ጥራታቸውን ጠብቆ ሐይቅ ከተማ አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ አቅርቦ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጪ አድርጐ ይወስዳል::
- የሚገዙት ዕቃዎች ጥራታቸው የተጠበቀ መሆን አለበት::
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-222-01 62 ደውሎ መጠየቅ ይችላል ::
በደቡብ ወሎ ዞን የሐይቅ ከተማ አስ/ገን/ኢኮ/ትብብር ጽ/ቤት
የግዥ፤ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን