የግንባታ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐይቅ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት ተጀምሮ ሳይጠናቀቅ የቆመውን የ1ኛ ፎቅ /የ1st ፍሎር/ ባለ5 የመማሪያ ክፍል ግንባታን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስጨረስ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታችያሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት መጫረት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽንተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈትቶችም፤
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለቸው፣የሚፈለግባቸውን የንግድ ግብር የከፈሉ፣ ያደሱ፣ የግብር ከፋይመለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ያላቸውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ለነዚህም መረጃ ማቅረብየሚችሉ መሆን አለባቸው
- ጨረታውን ያሸነፈ የውል ማስከበሪያ 10 በመቶ አስይዞ መ/ቤቱ በሚፈልገው የውል አይነት መስማማት የሚችልና
- የሙያ ምዘና የስራ ፈቃድ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ተጫራጮች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን በወቅቱ ነጻ ገበያ መሠረት መሙላት አለባቸው
- ደረጃ 8 /ስምንት/ BC/GC ግንባታ ሥራ ተቋራጭ እና በላይ የሆነና የ2011 ዓ.ም እና የቅርብ ጊዜ በተመሳሳይ ስራ የመልካም ስራ አፈጻፀም መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታ እንድሳተፍ ከገቢዎች ጽ/ቤት ከፍቃድ ሰጭ አካል ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስከ 21ኛው ቀን ድረስ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናቶች 11፡30 ድረስ ዘወትር በስራ ሠዓት ሐይቅ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትም/ቤት በመምጣት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ግንባታ ጠቅላላ ዋጋ የተጫረቱበትን 2 በመቶ በባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸጉ በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጨረታው ከወጣበት በ22ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ22ኛው ቀን 4፡00 ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ /ዝግ ከሆነ/ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡ በእለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ መጠቀምና አሻሚ ነገሮች ካሉ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች ከአብክመ ውጭ ከሆኑ በአማራ ክልል በሚገኙ ፍቃድ ሰጭ አካል የተሰጠ አጭር ጊዜ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት ግንባታ ጥለው ያልጠፉ፣ ያላቋረጡ፣ ክስ የሌለባቸው መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ይህ ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ለጨረታ ሲወዳደሩ ላወጡት ወጭ ትም/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0332220220 ወይም 0972430212 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሐይቅ ከፍ/ትም/መሠ/2ኛ ደረጃ ትም/ቤት