የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሴካ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/የግ ማህበር ለሰጠው የብድር ገንዘብ አመላለስ በመያዣነት የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 98/90 በተሰጠው ስልጣን መሠረት በግልፅ ጨረታ /ሐራጅ/ ባለበት ሁኔታ ለመሸጥ ይፈልጋል::
የተበዳሪው/ የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት አድራሻ |
የንብረት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት |
የሃራጁ መነሻ ዋጋ በብር |
የሃራጁ ደረጃ |
የሃራጁ ቀንና ሠዓት |
ሴካ አግሮ ፕሮሰሲንግ ኃ/የተ/ የግል ማህበር |
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት፣ ቤንች ሽኮ ዞን፣ ጉረ–ፈርዳ ወረዳ ፣ ጉጃ ቀበሌ |
የማንጎ እርሻ እንዲሁም የሩዝ ማቀነባበሪያ ማሽን ከነሙሉ ግንባታዎች ፤ ተሽከርካሪዎች፣ የእርሻ መሳሪያዎች እና ልዩ ልዩ መለዋወጫዎች |
2,714 ሄክታር የማንጎ እርሻ እና 4.61 ሄክታር የሩዝ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ |
199,376,460.19 (አንድ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ ስድስት ሺህ አራት መቶ ስልሳ ብር ከአሥራ ዘጠኝ ሳንቲም) |
የመጀመሪያ |
ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ ፤
- ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 25 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒ.ኦ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፤
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ላሐራጅ ሲቀርብ በሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል::
- በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረጋል::
- ሃራጁ የሚካሄደው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው፣ ተበዳሪው እናየሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች ብቻ በተገኙበት በተጠቀሰው ቀንና ስዓት ቤንች ሽኮ ዞን ጉረፈርዳ ወረዳ ጉጃ ቀበሌ በሚገኘው የእርሻ ቦታ ነው ::
- 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰነ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
- ፕሮጀክቱ እየሠራ ያለ በመሆኑ ምክንያት ለሥራው ተብሎ የተፈጸመ ግዢ ካለ በርክክብ ወቅት በሚደረስበት ግምት ገዢው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ ጨምሮ በመክፈል ንብረቱን ይወስዳል:: ነገር ግን በባንኩና በገዥው መካከል ስምምነት ካልተደረሰ ባንኩ በሚያመቸው መንገድ ንብረቶቹን የማንሳት መብት አለው::
- አንዳንድ የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች፣የእርሻ መሣሪያዎች፣ወዘተ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል ::
- ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው ከተቻለ ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ሲሆን አሸናፊው በባንኩ ብድር ፖሊስ መሠረት አስፈላጊውን መስፈርቶች ካሟላና የፕሮጀክቱን ሥራ የሚያስቀጥል ከሆነ ንብረቱን በከፊል ብድር ለመግዛት መጠየቅ ይችላል:: ነገር ግን በከፊል ብድር ለመግዛት የጨረታ አሸናፊው በራሱ ስም ወይም እራሱ 10%/አስር በመቶ/ ወይም ከዚያ በላይ የአክሲዮን ባለድርሻ የሆነበት የንግድ ማህበር ከግብር፤ከታክስና ከሌሎች ማናቸውም ዕዳዎች ነፃ መሆኑን ከሚመለከታቸው አካላት ማስረጃ በማቅረብ እንዲሁም ምንም ዓይነት የዕዳ ይከፈለኝ ጥያቄ ያልቀረበበት መሆን አለበት::
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኘሮጀክት ማገገሚያና ብድር ማስመለስ ዳይሬክቶሬት II በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-53-73 ደውሎ ማግኘት ይቻላል ወይም ከባንኩ ድህረ ገጽ www.dbe.com.et ማግኘት ይቻላል:: ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉም ካሉ ከዳሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ