የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEU/PLW & F/NCB-003/2012
የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው ቶነር ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ተቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ
|
የጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን
|
1 |
የተለያዩ መጠን ያላቸው ቶነር
|
23,402.50
|
መዝጊያ፡– ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ጠዋት መክፈቻ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት ጠዋት፡፡
|
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቶች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ግንቦት 12 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 በመምጣት የማይመለስ ብር ለሎት-1 ብር 400.00 (አራት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ሐረር ራስ ሆቴል ጀርባ የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ሪጅን ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ ፕሮኩዩርመንት ሎጂስቲክስ ዌር ሃውሲንግ እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 205፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ብር ለሎት 1 ብር 23,402.50 (ሃያ ሦስት ሺህ አራት መቶ ሁለት ብር ከሃምሣ ሣንቲም (50/00) በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ » እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር EEUPiw & F/NCB-003/2012 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ለሎት1- ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው ኣድራሻ ቢሮ ቁጥር 205 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለሎት- ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 025-466-08 43 መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት