የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር ..HTRDB RRCM 001/13
የሐረሪ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ከዚህ በታች ያሉትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን ለጨረታ ይጋብዛል፡፡
- የአገልግሎት ግዢው የሚፈልገው የፕሮጀክቱ አይነት የ50ኪ.ሜ (በቁጥር 9) የገጠር መንገዶች ዲዛይን፡፡
- ተጫራቹ የንግድ ዘርፉን የሚያመለክት የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለበት
- ተጫራቹ ግብር ምዝገባ ቁጥር ወይም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
- ተጫራቹ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን የሚያመለክት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት
- ተጫራቹ የግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በወቅቱ የተከፈለ መሆኑን የሚያሳይ ማረጋገጫ ማቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ሰነዱ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀናት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል መግዛት ይችላል፡፡
- ተጫራቹ የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 የባንክ ዋስትና ወይም የማይሻር ሌተር ኦፍ ክሬዲት የቀረበ ዋስትና ሊያቀርብ ይችላል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ አዳራሽ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጋዜጣ ከወጣበት ተከታታይ 21 ቀናት በኋላ በ22ኛ ቀን ይሆናል፡፡ ቀኑ ከሥራ ቀን ውጪ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥራችን 025 666 07 98 ወይም 09 85 093765 በመደወል ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት የሥራ ቀናት መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐረሪ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት ቢሮ