የጨረታ ማስታወቂያ
የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የሀረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሰራተኞች እና ለደንብ ማስከበር ጽ/ቤት የተለያዩ የደንብ ልብሶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች ለማቅረብ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ግብር መክፈያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያላቸው ፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ምዝገባ ፍቃድ ሰነዶችን ኮፒ በማድረግ የሚችል መሆን አለበት።
- ጨረታው ጸንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ (Bid bond) በጥሬ ገንዘብ፣ በሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሐ/ክ/መ የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 መክፈል መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾቹ የጨረታ መመሪያ መሰረት በማድረግ የመወዳደሪያ ጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በሐረር ከተማ የራሱ ድርጅት ያለው ወይም በከተማው ህጋዊ ወኪል/በውልና ማስረጃ የተወከለ/ አከፋፋይ እና መጋዘን ያለው መሆኑን ማቅረብ አለበት።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ተዘግቶ በ9፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት ይከፈታል።
- ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ጨረታው የሚከፈትበትና ለማብራሪያ ጥያቄ ዓላማ የሚያገለግል የሻጭ አድራሻ ፖስታ ቁጥር፡- 46 ፋክስ ቁጥር 025663707 ስልክ 0915756570
የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት