የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የሐረሪ ህዝብ ከልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ በ2013 በጀት ዓመት
- የተለያዩ የመማሪያ መጸሀፍቶችን ለማሳተም በሀገር ውስጥ ገበያ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታ ለመወዳደር የሚትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1.ተጫራቾች ማሟላት ያለባችሁ የቅድመ መወዳደሪያ መስፈርቶች፡-
- 1.1. በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- 2.2. የንግድ ፍቃደ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው
- 1.3 የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ
- 1.4 በአቅራቢዎች ምዝገባ ፍቃድ ያለው
- 1.5 የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈፀመ
- 1.6 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
2 በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በሐረሪ ህ/ክ/መንግስት ትምህርት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ን/አስ/ ስራ ሂደት ክፍል ብር 150.00 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) በመከፈል መወሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (bid bond) ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲፒኦ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጨረታ ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ ማስከበሪያው ይመለስላቸዋል፡፡
5 ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራቾች የሚቀርበትን የውድድር ጥያቄ ቢሮው አይቀበልም፡፡
6. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በቀጣይ ስራ በ4፡00 የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ በ4፡30 ሰዓት በሐረሪ ህ/ክ/ መንግስት ትምህርት ቢሮ ኣዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
7 ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
8 ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +2516660490 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት
ትምህርት ቢሮ