Disposal Sale / Materials / Metal and Metal Working / Other Metals / Other Sales / Tyres & Battery / Wood and Wood Working

የልደታ ክ/ከተማ የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ የተማሪመፅሐፍቶች፣ አሮጌ ቆርቆሮዎች ፣ የብረት በሮች ፣ መደገፊያ ያለው 1ወንበር ፣ የብረት በር ትልቁ፣ ጋሪ የብረት ጎማ የሌለው፣ የማይካ በኣሸንዳ፣የእንጨት ጠረጴዛ ትልቁ፣ የቆርቆሮ በር፣የእንጨት መስኮቶች፣ የብረት ዴስኮች፣ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ የብረት ወንፊት ወፍራሙ፣ የፓርከ ማጠሪያ ወፋፍራም ብረቶችን እና የቆርቆሮ አሸንዳዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የልደታ ክ/ከተማ የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ያገለገሉ

 • የተማሪ መፅሐፍቶች፣ አሮጌ ቆርቆሮዎች ፣ የብረት በሮች ፣ መደገፊያ ያለው ወንበር ፣
 • የብረት በር ትልቁ ፣ ጋሪ የብረት ጎማ የሌለው፣ የማይካ በኣሸንዳ፣ የእንጨት ጠረጴዛ ትልቁ፣
 • የቆርቆሮ በር ፣ የእንጨት መስኮቶች ፣ የብረት ዴስኮች ፣ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣
 • የብረት ወንፊት ወፍራሙ ፣ የፓርከ ማጠሪያ ወፋፍራም ብረቶችን እና የቆርቆሮ አሸንዳዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መመሪያ የማክበርና የመፈጸም ግዴታ አለባቸው።

 1. ተጫራቾች የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት አብነት አደባባይ ወደ ውስጥየሚወስደው አስፓልት አለሙ ሜዳ 100 ሜትር ገባ ብሎ የሚገኝ ሲሆን የጨረታ ሰነድ የሚገኝበት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ሲሆንጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከቀኑ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ::
 2. ተጫራቶች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ያገለገሉ የተማሪመፅሐፍቶች፣ አሮጌ ቆርቆሮዎች፣መደገፊያ ያለው የወንበር ፣የብረት በሮች ፣የብረት በር ትልቁ፣ ጋሪ የብረት ጎማ የሌለው ፣የማይካ አሸንዳ፣ የእንጨት ጠረጴዛ ትልቁ፣ የቆርቆሮ በር፣የእንጨት መስኮቶች፣የብረት ዴስኮች፣ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ የብረትወንፊት ወፍራም ፣ የፓርክ ማጠሪያ ወፋፍራም ብረቶችን እና የቆርቆሮ አሸንዳዎች ዘወትር በስራ ሰዓት ከ3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሱት መ/ቤቱ በመሄድ በአካል መመልከት ይችላሉ ነገር ግን የጨረታ ሰነዱን ያልገዛ ማየት አይችልም፣
 3. ተጫራቾች ከዚህ የጨረታ ሠነድ ጋር በተያያዘው የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ስማቸውን፣ የሚኖሩበት ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ፣ የቤት ቁጥርና ስልክ ቁጥራቸውን (ተለዋጭ ስልክ ቁጥሮችን ጨምሮ) በመግለጽና በመፈረም ማቅረብ አለባቸው:በገዢው ወይም በሕጋዊ ወኪሉ ያልተፈረመ መጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
 4. ተጫራቾች ሁሉንም ዕቃዎች ላይ ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው
 5. ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን የተለያዩ ያገለገሉ ፣ የተማሪ መፅሐፍቶች፣አሮጌ ቆርቆሮዎች፣መደገፊያ ያለው ወንበር ፣ የብረት በር ትልቁ፣ ጋሪ የብረት ጎማ የሌለው ፣የማይካ አሸንዳ፣ የእንጨት ጠረጴዛ ትልቁ፣የቆርቆሮ በር፣ የእንጨት መስኮቶች ፣የብረት ዴስኮች፣ ልዩ ልዩ ብረታ ብረቶች፣ የብረት ወንፊት ወፍራሙ፣ የፓርክ ማጠሪያ ወፋፍራም ብረቶችን እና የቆርቆሮ አሸንዳዎችን በጥቅል መጫረት ይኖርባቸዋል::
 6. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ ስም፣ አድራሻ እንዲሁም ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ንብረቱን የሚገዙበትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ጽፈውከፈረመ በኋላ በፖስታ አሽገው በኦሜድላ መ/ደ/ት/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው።
 7. ተጫራቹ በአሃዝ እና በፊደል በሰጠው ዋጋ ልዩነት ካለው ጽ/ቤቱ ከፍተኛውን ዋጋ ይወስዳል።
 8. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ9፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሜድላ መ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል:: ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም::
 9. ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በኋላ የሚደርሱ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት እይኖራቸውም።
 10. ዋጋ ለመስበርና በተለያየ መንገድ ፍትሃዊ ውድድር እንዳይኖር በነጠላ ወይም በቡድን በሚመሳጠሩት ላይ ጽ/ቤቱ ተገቢውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል።
 11. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው በጥቅል ሰተመደቡት ዕቃዎች ከፍተኛ ዋጋ ያቀረስ ይሆናል::
 12. ተጫራቾች ለኣንድ መደብ ንብረት ወይም በፕትል እኩል ዋጋ በመስጠት አሸናፊ ሲሆኑ እንደገና በማወዳደር አሸናፊው ይለያል፣ ድጋሚ ተመሳሳይ ዋጋ ከሰጡ አሸናፊው በእጣ እንዲለይ ይደረጋል። ነገር ግን ቀድሞ ከሰጠት ዋጋ በማሳነስ መወዳደር አይቻልም
 13. ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ለተቀመጠው የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሣጥኑ ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባትይኖርባቸዋል:: የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊ ለሆነት ስሚከፍሉት ዋጋ ውስጥ ይታሰብላቸዋል:: የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ | ሲፒኦ/ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል።
 14. ኣንድ ተጫራች ያቀረበውን የመጫረቻ ሰነድ ላይ ዋጋ ሲሞላ ስህተት ማድረጉን ካወቀ ማረሚያውን ከጨረታው መዝጊያ በፊት ማሻሻያ ወይም ማረሚያ በሚል በፖስታው ላይ በመጻፍ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል::
 15. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሰጠውን ዋጋ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም::
 16. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
 17. ከጨረታ መነሻ ዋጋ በታች እና መነሻ ዋጋ ሞልቶ ያቀረበ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል::
 18. ተጫራቶች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ከውድድሩ ሊወጡ አይችሉም።
 19. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ 5 የስራ ቀናት ውስጥ መክፈል ይኖርባቸዋል:: ሆኖም ሙሉ ከፍያው በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይደረጋል::
 20. አሸናፊ ተጫራቶች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ 2 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው
 21. ተጫራቶች በሚሰጡት ዋጋ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ወይም ስርዝ ድልዝ ካደረጉ በተስተካከለው ፊት ለፊት መፈረም አለባቸው::
 22. የጨረታ ሰነዱን 100.00 (አንድ መቶ ብር) በስሙ ያልገዛ ተጫራችበጨረታው ሊሳተፍ አይችልም ፤ ጨረታውን የሚካፈለው በወኪል ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል::
 23. የተሸጠ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ እይደረግም፡፡
 24. ፎቶ ኮፒ በተደረገ የጨረታ ሰነድ የተወዳደረ ተጫራች ከጨረታው እንዲሰረዝ ይደረጋል::
 25. አንድ ተጫራች ለጨረታ ለቀረቡት ንብረቶች ከአንድ ጊዜ በላይ የጨረታ ሠነድ በማስገባት መወዳደር አይችልም::
 26. በጨረታ ሂደቱ ላይ ቅሬታ ያለው ማንኛውም ተጫራች ቅሬታውን ለስራ ክፍሉ ማቅረብ ይችላሉ:: ሆኖም ያቀረቡት ቅሬታ ለት/ቤቱ አስተዳደር ማቅረብ ይችላሉ።

ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0112135189 መጠየቅ ይችላሉ::

ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የልደታ ክ/ከተማ የኦሜድላ የመ/ደ/ት/ቤት