የጨረታ ማስታወቂያ
የልደታ ክፍለ ከተማ የወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በጨረታ ቁጥር ል/ክ/ከ/ወ/9/ፋኢ/ል/ጽ/ቤት/01/13
- የተለያዩ አላቂ እቃዎችን፣
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፤
- የፅዳት እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡
- በጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በእቃ አቅራቢነት ዝርዝር በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2013 ዓም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በአጠቃላይ የእቃዎች ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 31 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸው እቃዎች አይነት ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ለማይቀርብላቸው እቃዎች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ቢሮ ቁጥር 9 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት ካላካተተ እንደተካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 9 ይከፈታል :: እለቱ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል ፡፡
- ወረዳው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
አድራሻ፡- አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ወረድ ብሎ ጥቁር አንበሳ የካንሰር ማእከል ፊት ለፊት፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0118591115
በልደታ ክፍል ከተማ የወረዳ 9 አስተዳደር ፋይናስ ኢ/ል/ጽ/ቤት