ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የላይ ጋይንት ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት በ2013 አመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ምድብ 1 የጽህፈት መሣሪያዎች
- ምድብ 2 የደንብ ልብስ/ ብትን ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ልብሶችን፣ ጃን ጥላ፣ የቆዳ ውጤቶች/
- ምድብ 3 የመኪና ጎማ
- ምድብ 4 ስፖርት ትጥቅ
- ምድብ 5 ኤልክትሮኒክስ ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅት መጫረት የሚችል መሆኑን እየገለጽን፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ ቲን ያላቸው፣
- የሚያቀርቡት እቃ/የሚሰሩት ስራ/ ከ200 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- የተጫራቾች በጨረታው ለመሣተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረበ አለባቸው፡፡
- የሚገዙት እቃዎች/የሚሰሩት ስራዎች/ አይነትና ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና/ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/ሲፒኦ/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /በመሂ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን ኦርጅናልና ቅጅ በማለት በተለያዩ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ላ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ለእቃዎች በ16ኛው ቀን በ3፡00 ይዘጋና በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ላጋ/ወ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታው ከመከፈቱ አይስተጓጐልም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊውን እቃዎች በየፑል ማድረስ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ መሆን የለበትም፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበትንና የሚከፈትበት የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ከመኪና ጎማ ውጭ የሌሎች እቃዎች ውድድሩ በሎት ይካሄዳል፡፡
- በማስታወቂያ ያልተገለጡ ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
- በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ላ/ጋ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0584450931/0584450005 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
የላይ ጋይንት ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት