ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የላይ አርማጭሆ ወ/ል/ከ/መ/ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ፣ አጠቃላይ የግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውመስፈርቶች፡-
- ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የ2012 ግብር የከፈሉ፣
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- ተጫራቾች በወረዳው የላይ አ/ወ/ል/ከ/ሙ/ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር ከእርእሰ መምህሩቢሮ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ሣይኖረው ዋናውና ቅጁ ተለይቶ በ2 ኮፒ ታሽጐ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሰነዱን በወረዳው የላይ አ/ወ/ል/ከ/መ/ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን ገንዘብ 1 በመቶ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብበጨረታ መክፈቻ እለት በፖስታው ውስጥ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሌተርኦፍ ክሬዲት ከሆነፀንቶ መቆያ ጊዜው ዘጠና ቀንና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን መግዛት ይችላል፡፡ የጨረታሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለበት እና ለመሰረዙ ልዩ ፊርማ ከሌለበት ውድቅ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ጋዜጣው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚያው ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በጠቅላላ ድምር ነው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ማወዳደሪያ ሰነድ ስማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈርአለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ንብረቱን ከወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ ማስገባት አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ኦርጅናል ያልሆነ እቃ ቢያቀርብ ውሉ የሚሰረዝ መሆኑ እና ያስያዘው የጨረታማስከበሪያ የሚወረስ መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡
- ጨረታው ሙሉ ወጭውን ያካተተ መሆኑን፣
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልጋቸው በስልክ ቁጥር 058 1160718 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
ማሣሰቢያ፡- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱየተጠበቀ ነው፡፡
የላይ አርማጭሆ ወ/ል/ከ/መ/ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት