የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የላልይበላ/ከ/እስ/ርከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት ስር የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን በCIP በታዘዘ በጀት የከባድ ማሽነሪ መኪናዎች ማለትም፡–
- ሎድር፣ ሮሎ ፣ ሲኖትራከ፣ ትራክተር መኪናዎች ጥገና የከባድ መኪና ጥገና ህጋዊ ፈቃድ ካላቸው ጋራጆች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማጫረት አወዳድሮ ካሽናፊው ጋር ውል በመያዝ ማስጠገን ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነበር/፣ የቫት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከሚጫረቱባቸው ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ከመጀመሪያው ቀን ከ5/3/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች/ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በላልይበላ ከተማ አስተዳደር ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት /የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀንከ5/03/2013 ዓ ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ድረስ በላልይበላ ከተማ አስተዳደር /ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት/የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በብር 50 /ሀምሳ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱ የገዙ ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን 1 ወይም ወጥ በሆነ 2 ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የላሊይበላ ከተማ አስተዳደር/ከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤትየግ/ፋይ/ንብ/አስ/ቡድን የጨረታ ኮሚቴው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ለሚሰራው የመኪና ጥገና ስራ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ጽ/ቤት በመቅረብ ቅድሚያ ውለታ መውሰድ አለበት፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን የመኪና ጥገና ስራ በተዘጋጀው የጥገና ዝርዝር መሰረት በጥራት ካላስረከበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ውርስ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ማብራሪያ/ማሻሻያ ጥያቄ ካላቸው ከጨረታው የጊዜ ገደብ ከ10 ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆዩበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ40 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በፊት ጨረታ አሸናፊ ሆነው እንደውላቸው ያላጠናቀቁ ወይም ከታወቀ ተቋም ዕገዳ የተደረገባቸውን አያሳትፍም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ሊሞላ የጨረታ ሰነዱ ላይ ዋጋ ሳይሞሉ ክፍት ማድረግ ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ መሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ የግ/ፉይ/ንብ/አስ/ር ቡድን ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 03333360016 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የላልይበላ/ከ/እስ/ርከ/ል/ቤ/ኮ/አገ/ት/ጽ/ቤት