የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በምስራቅ ሸዋ ዞን የሉሜ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በ2013 የበጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶች የሚያገለግል የተለያዩ
- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- አላቂ የጽዳት እቃዎች ፤
- ቋሚ አላቂ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ (ማለትም ኮምፒውተር እና ፕሪንተር)፤
- የቢሮ ቋሚ እቃዎች (furniture) ፤
- የመኪና እና ሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች፤ እና
- የሰራተኞች ደንብ ልብስ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአነስተኛና ጥቃቅን ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ, ከግል አቅራቢዎች እና ድርጅቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው ለምትሳተፉ ተጫራቾች ፦
- በመስኩ ለመሰማራታችሁ እና እቃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ ከፌዴራል ወይም ከክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ሊስት ላይ የተመዘገቡ ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናችሁ የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር ማለትም የ2012 ዓ.ም የከፈሉና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን ጊዜው ያላለፈበት የተሠጣችሁን ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጽህፈት መሳሪያዎች ብር 10,000 (አስር ሺ)፣ ለጽዳት እቃዎች ብር 6,000(ሰድስት ሺ)፣ ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ብር 10,000 (አስር ሺ ) ፣ ለፈርኒቸር እቃዎች ብር 7,000(ሰባት ሺ) ፣ ለመኪና እና ሞተር መለዋወጫ ዕቃዎች 3,000(ሶስት ሺ) እና ለደንብ ልብስ ብር 6,000(ሰድስት ሺ) ለሉሜ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ብለው በማጻፍ በባንክ በተረጋገጠ CPO ለየብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- አነስተኛና ጥቃቅን ማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ደብዳቤ ካደራጃችሁ መስሪያ ቤት በሉሜ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ ቤት ስም በማጻፍ ለምትወዳደሩባቸው ዕቃዎች ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባችኋል። ሆኖም የድጋፍ ደብዳቤ ተብሎ ተጽፎ የሚቀርብ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት የለውም።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ዋስትና ቢያንስ ለ28 ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15/12/2012 ዓ.ም የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ( ሁለት መቶ )ብር በመክፈል ከሉሜ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ እስከ 5፡00 ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በገዙት የጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት የድርጅቱ/የማህበሩ/የግለሰቡ ኃላፊ ፊርማ፣ ስምና ማህተም ያረፈበትን እያንዳንዱን ሰነድ ለየብቻ ዋናውንና ኮፒውን በተናጠል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 15/12/2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡30 ድረስ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 6 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በ15/12/ 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡35 ታሽጎ በዚያኑ እለት ከጠዋቱ 5፡45 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ፡፡
- በደንብ ልብስ ላይ የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የእያንዳንዱን ልብስ እና ጫማ ናሙና ይዘው በመቅረብ መወዳደር ይኖርበታል።
- አሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ በማስታወቂያ የሚገለጽ ሲሆን ላሸነፈባቸው እቃዎች የጠቅላላውን ድምር 10% ለውል ማስከበሪያ CPO/Bank grantee ማስያዝ ይኖርባችኋል፡፡
- በፈርኒቸር ላይ የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች እያንዳንዱን ወንበር ፣ጠረጴዛ በጨረታ ሰነድ ዝርዝር መሰረት በፎቶ የተደገፈ ናሙና ይዘው በመቅረብ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው ማህበር/ድርጅት/ግለሰብ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ሲሆን ላሸነፈባቸው እቃዎች የጠቅላላውን ድምር 10% ለውል ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
ስልክ ቁጥር 0221160042/0221160509/022116052
የሉሜ ወረዳ ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት
ሞጆ