ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2013 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማቴሪያሎች በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ከተ.ቁ 1-8 ባለው ዝርዝር መሰረት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- የጽህፈት መሳሪያ
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
- የፋብሪካ ማቴሪያሎች
- የሞተር ሳይክል እቃዎች
- የደንብ ልብስ
- የጽዳት እቃዎች
- የስፖርት ትጥቅ
ስለዚህ:-
- በየዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነበር)ያላቸው እና ከ200,000 ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
- ተጫራቾች ከተራቁጥር 1 -8 ለተጠቀሱት ዕቃዎች የመረጃቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በለገሂዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ብሎክ 1 ቢሮ ቁጥር 2 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50/ሃምሳ ብር/በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም ፊርማ ስም በግልጽ በማስቀመጥ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ለለገሂዳ ወረዳ ገ/ኢ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ብሎክ 2 ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ ይቆያል፣
- ጨረታው የሚታሸገው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ቀን 4፡30 ጨረታው ይከፈታል፣
- ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚወዳደረው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ሙሉ በሙሉያልሞላ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከመውሰዱ በፊት መ/ቤቱ የጠየቀውን የዕቃ ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ወጭ ለገሂዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ባሉት መ/ቤቶች በየንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም አሸናፊ ዕቃዎቹን ርክክብ ሲፈጽም ጥራቱን በባለሙያ ተረጋግጦ የታሸጉ ዕቃዎችን ተፈተውና ታይተው ተቆጥረው ተለክተው ገቢ መሆን አለባቸው፣ ጥራታቸውን ያልጠበቁ ከሆነ በ5 ቀናት ውስጥ መልሶ መተካት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች አሸናፊነቱ ከተገለጸ በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ ውለታውን በመውሰድ የውለታ ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለበት፣
- የጨረታ ማሸጊያና መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ/የህዝብ በዓላት/ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች በሚሞሉት የዕቃ ዋጋ ላይ መለኪያና ጥራቱን ጠብቀው መሙላትና ማቅረብ አለባቸው፣
- የጨረታው መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት ማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል እንደማይችሉ ሆኖ በውለታ ሰነድ ላይ ዝርዝሩ ይቀመጣል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች የሚያቀርባቸው ዕቃዎች ጥራት ያለው እና ኦርጅናል መሆን አለበት፡፡
- በየዘርፉየግድ ፍቃድ ለሚጠይቁ በየዘርፉ ካላቀረበ ከጨረታ ውጭ ይደረጋል፡፡
- በመመሪያው መሰረት 2% ታክስ የሚቆረጥ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0338922316 ወይም በአካል በመገኘት አገልግሎት ያገኛሉ፡፡
- የወረዳችን ከተማ ከደ/ወሎ ዞን ምዕራብ አቅጣጫ በ103 ኪሜ ላይ ትገኛለች፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለናሙና ያስቀመጥናቸውን እቃዎች ከግዥ ቢሮ በአካል በመቅረብ መመልከት ይችላሉ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት
በደቡብ ወሎ መስ/ዞን የለገሂዳ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ወይን አምባ