1ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
የሆሣዕና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት ቀጥሎ የተመለከቱትን የማስተማሪያ እና የቢሮ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
1. በአውቶሞቲቭ ቴክኖሎጂ ዘርፍ
- 1.1. የተለያዩ ስፔር ፓርቶችን፣ F1 Engine፣ ሞተር ሳይክሎችን እና አክሰሰሪዎችን
2. በኤሌክትሮኒክ ዘርፍ
- 2.1 የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችንና ኢንዳስትሪያል ማሽኖችን
3 በኤሌክትሪሲቲ ዘርፍ
- 3.1 የተለያዩ የኤሌክትሪካል ኢንስታሌሽን ዕቃዎችንና ማሽኖችን
4 በኮንስትራክሽን ዘርፍ
- 4.1. የግንባታና የአርማታ ሥራ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን/ማሽኖችን
- 4.2 የሳኒተሪ ኢንስታሌሽን ሥራ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን/ማሽኖችን
- 4.3 የሰርቨይንግ ቴክኖሎጂ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን/ማሽኖችን
- 4.4 የሮድ ኮንስትራክሽን ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን
- 4.5 የካርፔንተሪና ጆይነሪ ዕቃዎችንና ማሽኖችን
- 4.6 የፈርኒቸር ሥራ ዕቃዎችንና ማሽኖችን
5. በብረታ–ብረት ቴከኖሎጂ ዘርፍ
- 5.1. የተለያዩ ብረታ–ብረቶችንና መሳሪያዎችን
- 5.2 የብየዳ ማሽኖችን
- 6. የፅህፈት፣የድራፍቲንግና የላይብራሪ ሳይንስ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን
- 7. ኮምፒውተርና የኮምፒውተር ዕቃዎችንና አክሴሰሪዎችን
- 8. ለሆቴል እና ቱሪዝም የሚያገለግሉ ዕቃዎችንና መሳሪያዎችን
- 9. የቢሮ ጽዳት/ውበት እና አላቂ ዕቃዎች
- 10. አርባን ግሪነሪ (የከተማ ማስዋብ) ዕቃዎችንና ማሽነሪዎችን
- 11. የፋሽን ዲዛይንና ጨርቃ–ጨርቅ ዕቃዎችንና ማሽነሪዎችን
- 12. የሠራተኞች ደንብ ልብስ
ማሳሰቢያ
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቦታ አዲስ አበባ ተግባረ ዕድ ፖሊ ቴክኒከ ኮሌጅ እና በሆሣዕና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ቀን ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ10ኛው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ሆኖ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር ብቻ) በመከፈል መግዛት ይቻላል፡፡ ጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን የሥራ ቀናት ሆኖ እሁድንና የበዓል ቀናትን አይጨምርም፡፡
- የጨረታው ሣጥን የሚታሸገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ልክ 6፡00 ሰዓት ሆኖ ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ከሰኞ ይዞራል፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የዕቃ አቅራቢነት ሰርተፊኬትና ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሎት ወይም ሰነድ በሚገዙት ጨረታ ለእያንዳንዳቸው በባንክ የተረጋገጠ CPO ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም አሸናፊ ተጫራች ያሽነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ CPO ለውል ማስረከቢያ ማስያዝ ይጠበቃል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ያሽነፈውን ዕቃ ፣ እቃዎች፣ መሳሪያዎችንና ማሽነሪዎችን እስከ ኮሌጁ ድረስ በራሱ ወጪ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ኦርጅናል ዶክመንት 1 ፣ ፋይናንሻል ዶክመንት 1፣ ቴክኒካል ለየብቻ እና ኮፒ 2 ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
- ተጫራቾች ለበለጠ መረጃ 0465552655 ወይም 0465552659 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
የሆሣዕና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ