Computer and Accessories / Equipment and Accessories / Garment and Leather / Garments and Uniforms / Office Furniture / Office Machines and Accessories / Shoes and Other Leather Products / Textile

የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 የበጀት ዓመት ኤሌከትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር ፣ ደንብ ልብስ እና ጫማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ 

የሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2012 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ በከተማ አስተዳደሩ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

 • ሀ, ኤሌከትሮኒክስ፣ 
 • ለ. ፈርኒቸር፣ 
 • ሐ. ደንብ ልብስና ጫማ 
 1. በዘርፍ ወይም በንግድ ሥራ መስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ስግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ እንዲሁም የግብር ከፋት መለያ ቁጥር(Tin number) የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ የሆኑ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ 
 2. ተጫራቾች በኣቅራቢት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ፣ 
 3. የግዥው መጠን ብር 50,000.00/ሃምሣ ሺህ ብር እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት (vat)ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፣ 
 4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱበትን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡ 
 5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ዝርዝር /specification/ ከመደበኛ ጨረታ ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ:: 
 6. ከላይ ለተጠቃሚ ጨረታ ለእያንዳንዱ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን በሥራ ሰዓት ከሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 መግዛት ይችላሉ። 
 7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ብዛት ጠቅላላ ዋጋ ድምር 15.000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ ከባንክ የተረጋገጠ በክፍያ ትዕዘዝ /ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማሰያዝ። አለባቸው። 
 8. ተጫራቶች ሎሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናሉ እና ፎቶ ኮፒ ጨረታው ከመጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 3-4 ስዓት ድረስ ሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ፋኢ/ል/ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ:: 
 9. ጨረታ የሚዘጋው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሣዕና ከተማ አስተዳደር ሕንፃ 2ኛው ፎቅ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 23 ይከፈታል፡፡ የሚከፈተውም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ 
 10. መ/ቤቱ ስለግዥ እፈጻጸሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። 
 11. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ከጨረታው ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊትም በመዛባቱ ምክንያት እንዲከሰሱ ይደረጋል፣ያስያዘው የጨረታ ማስከበርያ ይወረሳል፡፡
 12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- 0916838549 ወይም 0916839347 በዚህ ቁጥር ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ። 

ሆሣዕና ከተማ አስተዳደር 

ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት