ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው ቁጥር 001/2013
የሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ በ2013 የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ለኮሌጁ ሥራ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በመደበኛ በጀት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የመኪና ጥገና በሚመለከት
- ሎት 2 የደንብ ልብስ ጨርቅ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ የወንድና የሴት አጭር ቆዳ ጫማዎች
- ሉት 4 የመኪና ጎማና መለዋወጫ ዕቃዎች
- ሎት 5 የተዘጋጀ የደንብ ልብስ የወንድና የሴት
- ሎት 6 የደንብ ልብስ ስፌት (ሆሳዕና መም/ ት/ኮሌጅ ግቢ ድረስ መጥተው ማሰፋት የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
- ሎት 7 አላቂ የትምህርት ጽ/መሣሪያዎችና የስፖርት ዕቃዎች፡፡
- ሎት 8 የጽዳት ዕቃዎች፡፡
- በዘርፉ ወይም በንግድ ሥራ መስኩ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልጽ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢ የተሰጠ ማስረጃ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ፣
- የግዥው መጠን ብር 50, 000 ሃምሣ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የማይመለስ ለእያንዳንዱ 50.00/ሃምሣ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ቀን በሥራ ሰዓት ከሆሣዕና መምህራን ትም/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 13 ማግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የሎት 1 እና ሎት 4 እያንዳንዳቸው ብር 10,000.00 እና ሎት 2፣ ሎት 3፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት 6፣ ሎት 7 እና ሎት 8 ለእያንዳንዱ ብር 3000.00 በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ድረስ ሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ዕለት በጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆሣዕና መምህራን ትም/ኮሌጅ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የሚከፈተው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ኮሌጁ ስለግዥ አፈጻጸሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ የሚሆኑ ሲሆን ወደፊት በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋል፡፡ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያም ይወረሳል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0465552650 ወይም 04655526552 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሆሣዕና መምህራን ትምህርት ኮሌጅ