ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር 001/2013
በላፍቶ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2013 በጀት ዓመት
- የተለያዩ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች፣
- አላቂ የጽዳት ዕቃዎች ፤
- የጥገና ዕቃዎች፣
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና
- ሌሎች ቋሚና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች -7064.78 CPO
- ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች– 8000 CPO
- ሎት 3ቋሚ እቃዎች– 2200 CPO
- ሎት 4 የእስፖርት እቃዎች-600 CPO
- ሎት 5 የደንብ ልብስ— 9000 CTO
- ሎት 6 የጥገና ሥራ ዕቃዎች -2000 CPO
- ሎት 7 የህትመት ሥራዎች____400 CPO
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡
- 1ኛ በጨረታ ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- 2ኛተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎቶች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ከጨረታው ሰነዳቸው ጋር ከላይ በተገለፀው መሰረት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
- 3ኛተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ላ/ን/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኝ የህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 37 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- 4ኛ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 5ኛ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በአስራ አንደኛ ቀን በ 11፡30 ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 37 ይከፈታል፡፡የመክፈቻው ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- 6ኛ. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፈት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ ሎት 2 ሎት፣ ሎት 4 ሎት 5 እና ሎት 6 ሎት7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 3 በመ/ቤቱ በቀረበው እስፔሲፊኬሽን መግለጫ መሰረት ሲሆን ስለማቅረባቸው በመ /ቤቱ በቀረበው እስፔሲፒኬሽን ላይ ፊርማ እና ህጋዊ ማህተማቸውን ተመቶ መመለስ አለባቸው፡፡
- 7ኛ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል
- 8ኛ. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተሰለ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
- 9ኛ. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸንፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
- 10ኛ. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡–ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ህዳሴ የመ/ደ/ት/ቤት ሃይሌ ጋርመንት ፊት ለፊት በሚወስደው አስፓልት
ሀጫሉ አደባባይ ከፍ ብሎ ኦሮሚያ ኮንደምኒየም ጀርባ፡፡ ስልክ ቁጥር፡– 011-84-95368/011-84-90005
ህዳሴ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት