የጨረታ ማስታወቂያ
የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ የላቦራቶሪ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸወን የተወጡና የመንግሥት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ (Website) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ከታውቀ ባንክ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼክ/የባንክ ዋስትና በጥሬ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ሳጥን እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ሆኖ ዕለቱ ቅዳሜና ዕሁድ/በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታውም በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ሲሆን፤ ዕለቱ በዓል/የዕረፍት ቀናት ውስጥ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ይህ ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ዘጠና ቀናት ነው፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡-(046)22126 47/212126 (046)220 26 47
ፋክስ፡– (046)220 61 63 221 24 73
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ
የመ.ሳ.ቁ.05
Website!- WWW.hu.edu.et
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ