የጨረታ ማስታወቂያ
የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
- ሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ
- ሎት 2 የፅዳት ዕቃ
- ሎት 3 የደንብ ልብስ
- ሎት 4 የመኪና መለዋወጫ
በግዥ መለያ ቁጥር HU/MHSC/NCB/2/3/4/5/2013 አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ–ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር የተመዘገቡ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መክፈቻ ዕለት ከጠዋቱ 2፡30-11፡00 ሰዓት በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ሃዋሳ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ ለእያንዳንዱ ሎት 10,000.00 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡ ከሲፒኦ ውጪ የሚመጣ ማንኛውንም የጨረታ ማስከበሪያ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስራ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአስራ አምስተኛው የሥራ ቀን ሆኖ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡20 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በዚሁ ቀን 8፡30 በኮሌጁ ሕንፃ ግዥና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ለጨረታው የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡ የሚቀርቡ ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስቁ፡– 046-212 01 20/046 820 92 88
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ