የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን 20 ላፕቶፕ እና 2 ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ከእነ ፕሪንተሩ እና ዩፒኤስ ባለ 1000V በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Tender
< Back

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን 20 ላፕቶፕ እና 2 ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ከእነ ፕሪንተሩ እና ዩፒኤስ ባለ 1000V በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

የጨረታ ማስታወቂያ

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን 20 ላፕቶፕ እና 2 ዲስክቶፕ ኮምፒውተር ከእነ ፕሪንተሩ እና ዩፒኤስ ባለ 1000V በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ ጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ::

  1. ተጫራቾች 2012 የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ሰርተፍኬት እና ከግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ከግብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ ቢያንስ እስከ ጨረታው መክፈቻ ዕለት  ድረስ የሚያገለግል መሆን የሚኖርበት ሲሆን የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈበትን የድጋፍ ደብዳቤ  የሚያቀርብ ተጫራች የጨረታው ይሰረዛል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮርፖሬሽኑ የሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 300-600 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 800-1100 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 312 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት ከጠዋቱ 430 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም በሲፒኦ በመ/ቤቱ የእንግሊዝኛ ስም Audi Services Corporation ስም ብቻ አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1o የሥራ ቀናት ቅዳሜን አይጨምርም፤ ክፍት ሆኖ በ11ኛው የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከጠዋቱ 500 ሰዓት በኮርፖሬሽኑ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  7. /ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 553 79 29/ 00553 7927 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ፡ የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ

ካዛንቺስ ከዘመን ባንክ ጐን /ከኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ፊት ለፊት/

ስልክ ቁጥር 01 553 79 29/ 00553 79 27

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ኮርፖሬሽን