የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴክተሮችና መምሪያዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት፡-
- ሎት1 – የጽህፈት መሣሪያና
- ሎት 2 – የጽዳት ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች፡-
- 1ኛ በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- 2ኛ. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
- 3ኛ. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት
- 4ኛ. የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፡–
በሀድያ ዞን መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 ቁጥር በእካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100/ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 10,000/አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 0461784281 /0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግሥት የሀድያ ዞን
ፋይናንስ መምሪያ ሆሳዕና