የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ጽ/ቤት የሀደሮ ከተማ አስ/ር ለሴ/መ/ቤቶች
- የኤሌክትሮኒክስ እና
- የጽ/መሳሪያ ዕቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ በዘርፉ ከተሰማሩት አቅራቢዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት፣ በአቅራቢዎች ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት፣ እንዲሁም የግብር ከፋዮች መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ጥሪ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ሀ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ቢሮ ቁ01 የጨረታ ሰነዱን በ200 ብር ብቻ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የዋጋ ቅናሽ (Discount) እስካልተጠቀሰ ድረስ የዋጋ ቅናሽ ብሎ መሙላት ቅናሹ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ፣በጥሬ ብር፣ በኢንሹራንስ እና በቦንድ በማስያዝ ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ (ሁሉንም የህጋዊነት ዶክመንቶችን፣ ሲፒኦ እና የሥራ ዝርዝርና ዋጋን የያዘ) በሁለት ፖስታ ለየብቻ በማሸግ በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባችኋል።
- ይህ ጨረታ የሚከፈተው በ15/03/2013 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30 ሠዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው በተገኙበት ከሰዓት 9፡00 ሰዓት በጽ/ቤታችን ግ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ቁ.1 ይከፈታል።
- የሂሳብ ስህተት ከ2% ባላይ ከሆነ ከውድድሩ ውጭ ያደርጋል፡፡
- ተጫራቾች በመክፈቻ ስርዓት ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎችን በአጭር ጊዜ አጠናቀው ማስረከብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- አንድ ተጫራች ሌላው ያቀረበውን ዋጋ መነሻ በማድረግ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሀደሮ ከተማ አስ/ር ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት
/ሀዳሮ/