ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ፡
- የጽዳት ዕቃዎች
- የእስቴሽነሪ ዕቃዎች ግዥ
- የፈርኒቸር ዕቃ ግዥ እና
- የደንብ ልብስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ
ተጫራቾች፡–
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO 5000(አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለእያንዳንዱ በሆስፒታሉ ስም ማሰራት አለባቸው::
- የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ ለየብቻ ፋናንሻልና ቴክኒካል ብሎ በፖስታ ላይ መጻፍ ይኖርባቸዋል፤ CPO ያለበት ፖስታ ለብቻ መኖር አለበት፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው በ16ኛ ቀን ጠዋት ከ3፡00 እስከ 8፡00 ሰዓት በሀዌላ ቱላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በግዥና ክፍያ ክፍል ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡ ሆኖ ጨረታው በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ እንዲሁም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፤
- ጨረታውን ያሸነፈ ድርጅት ከመ/ቤቱ ጋር ውል ከገባ በኋላ ዕቃውን እስከቦታው በማቅረብ በሞዴል 19 ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 0462290361/0924302087/0917836497
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት
በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የሀዌላ ቱላ
የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል