ግዥ መለያ ቁጥር የላቦራቶሪ ዕቃዎች HU/ NCB/36/02/2012 BY
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የላቦራቶሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግሥት መ/ቤቶች ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና የመንግሥት በጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ Website) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የከፍያ ማዘዣ ቼክ/የባንክ ዋስትና በጥሬ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ሳጥን እስከ ሚከፈትበት ቀን ድረስ አዘጋጅተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ሆኖ ዕለቱ ቅዳሜና እሁድ/በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታወም በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ሲሆን ዕለቱ በዓል/የእረፍት ቀናት ውስጥ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ይህ ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ዘጠና ቀናት ነው፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር፡-(046)22126 47/212126 (046)22026 47
ፋክስ፡-(046)220 5163 22124 73
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የመ.ሳ.ቁ 05
Website!- WWW.hu.edu.et
ሀዋሳ
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ