የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር HU/MCC/NCB/03/01/2013-BY
የግዥ መለያ ቁጥር HU/MCC/NCB/04/02/2018-BY
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ኮሌጆች በግዥ መለያ ቁጥር HU/MCC/NCB/03/01/2013-BY ፡
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ቶነር፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- ኤሌከትሮኒክስ፣
- ፈርኒቸር፣
- የስፖርት መገልገያ ቁሳቁስና ትጥቅ እና
- የሰራተኞች የደንብ ልብስ፡፡
እንዲሁም
በግዥ መለያ ቁጥር HU/MCC/NCB/04/02/2013-BY
- ኬሚካልና የቤተ–ሙከራ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
1 ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ ከፈዴራል ሀገር ውስጥ ገቢ ወይንም ከሌሎች ግብር ሰብሳቢ የመንግስት መ/ቤቶች ወቅታዊና የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በመንግስት ጨረታዎች መካፈል የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ፣ በፌዴራል ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የመረጃ መረብ (Website) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ እና የሚጫረቱበት ዋጋ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) የሚበልጥ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2 ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 50,000.00 ( አምሳ ሺህ ብር) ለኬሚካል እና የቤተመከራ ዕቃዎች እንዲሁም 15,000.00 (አስራአምስት ሺህ ብር) የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎችቶነርየፅዳት ዕቃዎች ኤሌክትሮኒክስ ፈርኒቸር የስፖርት መገልገያ ቁሳቁስና ትጥቅ እና የሰራተኞች የደንብ ልብስ ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ ሎት (LOT) በባንክ በተረጋጠ ቼክ ወይም CPO የጨረታው ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሠነድ ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋና ግቢ ህንጻ ቁጥር 132 በሮቁጥር 18 ከኮሌጆች ግዥናንብረት አስተዳደር ቡድን መግዛት ችላሉ፡፡
4 ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ ኦርጂናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ድረስ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋ/ግ/ግዥና ንብረት አስተ/ ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ ጨረታው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡10 ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋ/ግ/ኮ/ግዥ/ንብ/አስተ/ቡድን መሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ግን ዕለቱ ቅዳሜ እና እሁድ /አገር አቀፍ በዓል/ ከሆን በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡10 ሰዓት በተጠቀው ቦታ የሚከፈት ይሆናል።
5 ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የዋናው ግቢ ኮሌጆች የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን
ስልክ ቁጥር፦251 468 224 033
251 462 211936
ፋክስ፡-251 462 205 163
ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ
የመ.ሳ.ቁ 05
Website!-www.hu.edu.et
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
የዋና ግቢ ኮሌጆች