የጨረታ ማስታወቂያ
የኦዲት ምርመራ የግዥ መለያ ቁጥር ግፋ/12/2012
የሀዋሳ ከተማ መው/ፍ/አገ/ድርጅት ከ2011 እስከ 2013 በጀት ዓመት ድረስ ያለውን በድርጅቱ የተንቀሳቀሰውን ሂሳብ በውጭ ኦዲት ለማስመርመር በጨረታ አወዳድሮ ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ የውጭ ኦዲተሮች ማሟላት ያለባቸው በኢትዮጵያ ሂሳብ አዋቂዎች እና ኦዲተሮች ቦርድ የሞያ ፈቃድ እና ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የ2012 ዓ.ም የዘመኑ ግብር
- የተከፈለበት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ በጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ዋስትና ማስያዣ ብር 30,000.00 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ግዥውን በሚፈፅመው ድርጅት ሥም ተዘጋጅቶ ማቅረብ ይኖርበታል:: ከተጠየቀው ሲፒኦ ማስያዣ ውጪ የቀረበ ጨረታ ውድቅ ይደረጋል፡፡
- የተዘጋጀውን ዝርዝር የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብር) በመክፈል ከሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ግዥ/ን/አስ/ከ/ቲ/አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 19 ሦስተኛ ፎቅ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ቴክኒካሉ እና ፋይናንሻል ለየብቻ ለእያንዳንዱ ሁለት ኮፒ በተለያየ ኤንቨሎፕ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንቱን ለመግዛት ሲመጡ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኮፒ ይዞ መምጣት አለበት ንግድ ፍቃድ ካልያዙ የጨረታ ዶክመንት አይሸጥም፤
- ዝርዝር ጉዳዮችና መመሪያዎች ተዘጋጅቶ በሚሸጠው የጨረታ ዶክመንት ላይ ተገልጿል፣
- ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 11.00 ሰዓት ድረስ ሀዋሳ ከ/መ/ው/ፍ/አገ/ድርጅት ግዥ/ን/አስ//ቲ/አስተባባሪ ቢሮ ቁጥር 19 በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:: ጨረታው በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀዋሳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 21 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
ስልክ ቁጥር፡046 212 1580/ 046 2128826
ድርጅቱ የሚገኝበት አድራሻ፡ከወልደ አማኑኤል አደባባይ በግራ በኩል ወደ አዲሱ መናኸሪያ በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር
ከአዜብ ዲያግኖስቲክስ ማዕከል አጠገብ
የሀዋሳ ከተማ መጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት