የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01
የሀዋሳ ተግባረ ዕድ ቴከኒክና ሙያ ት/ት ስልጠና ኮሌጅ ለ2013 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የተለያዩ ዓይነት በግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት፡ –
- ሎት 1 አላቂ የጽ /መሣሪያ
- ሎት-3 ደንብ ልብስ
- ሎት-23 የተሽከርካሪ ጥገና
ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/ትችል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሀዋሳ ተግባረ–ዕድ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በመቅረብ እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00(ሃምሳ ብር) ብቻ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ሞልተው ኦሪጅናሉንና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ላቀረቡት ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (ጥሬ ብር) ከኦርጂናል ዶከመንት በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በሀዋሳ ተግባረ–ዕድ ቴከኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ስም መሰራት አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ወቅት ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል፡፡
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት (እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ) ውስጥ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት/ኣካል ዕቃውን በኮሌጁ ንብረት ክፍል አምጥቶ ገቢ ሲያደርግ ብቻ ክፍያው የሚፈጸም መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፡፡
- ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 16 ግ/ፋ/ን/ አስ/ደ/ስራ ሂደት ይከፈታል፡፡
- ዋጋ የሚሞላው ከኮሌጁ በገዛችሁት ሰነድ ላይ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 046 212 25 35/0916108360/0928982927
የሀዋሳ ተግባረ–ዕድ ቴክኒክና
ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ